የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና
የጽ/ቤት ሃላፊ መልዕክት
ውድ የ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት አመራሮች፤ ሰራተኞች፤ ባለድርሻ አካላት እንደሁም የንግዱ እና ሸማቹ ማህበረሰብ በየጊዜው አለማችንና አገራችንን እየፈተነ የሚገኘውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የግብይቱም ይሁን የቁጥጥር ዘርፍ ተልዕኮውን ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላችሁን እየተወጣችሁ መሆኑን እገነዘባለሁ፡፡ ስለሆነም በግብይቱ ዘርፍ የምርት አቅርቦቱን በማስፋትና የገበያ ትስስሩን የማጠናከር፤ በቁጥጥር ዘርፉ ፍትሃዊ የንግድ ስርአትን የማስፈን፤ የህገ-ወጥ ነጋዴን ተፅዕኖ በመከላከል የ ክ/ከተማችንን ማህበረሰብ የኑሮ ጫና የማቃለል፤ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በመከላከል፤ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና በ2018 በጀት አመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሙሉ ጊዜያችንን ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን፡፡ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ከወረቀት ነፃ በሆነ ኦንላይን መሆኑና ሌሎች አገልግሎቶችም ወደ ቴክኖሎጂ ለማምጣት ቀልጣፋ፤ ወጪ ቆጣቢና ከሙስና ከብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን ለማድረግ እየሰራን እንገኛለን፡፡ ይሁን እንጂ የከተማችን የኑሮ ውድነት ችግርን የመቅርፍ፤ ብልሹ አሰራርን የመከላከልና አገልግሎት አሰጣጥን የማሻሻል፤ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ሙሉ ለሙሉ ፈተናል ማለት አንችልም በርካታ ስራዎች ይጠብቁናል፡፡ ጽ/ቤታችን በሕግ የተሰጡትን ተግባራት መወጣት እንዲችል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅበትን የጋር ሃላፊነት በመወጣት ለስኬቱ የድርሻውን እንዲያበርክት ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ በመጨረሻም በቢሮም ሆነ በመንደር ንግድ ህገ- ወጥነት ተግባር ሲታይ በነጻ ስልክ መስመር 8588 በመደውል ጥቆማ በመስጠት ከጎናችን እንድትሆኑ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡
አቶ ያሲን መሃመድ
የ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ንግድ ፅ/ቤት ሃላፊ
የጽ/ቤቱ ሃላፊዎች
ያሲን መሐመድ ኤልያስ
የንግድ ፅ/ቤት ሃላፊ
ብርሃኑ ዲዳ ንጉሴ
የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ቡድን መሪ
አበራ ድንቄ ቼገን
የንግድ ግብይት ማስፋፊያ ቡድን መሪ
ማርታ መንግስቱ አለሙ
ንግድ ምዝገባና ፍቃድ ደንበኞች አገልግሎት ቡድን መሪ
አየለች ሸጌ ተመስገን
መደበኛ ያልሆነ ንግድ ስርዓት ማስያዝ ቡድን መሪ
ኩምሳ በጅጋ ፈይሳ
የሸማቾች መብት ጥበቃ ቡድን መሪ
አስናቀች ግዛዉ ወ/አማኑኤል
የገበያ መረጃ ቡድን መሪ
ፀሐይ አስማረ አበጀ
የገበያ ማዕከል ልማትና አስተዳደር ቡድን መሪ
ራእይ
በ2022 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ ዘመናዊ፣ ፍትሃዊና ተወዳዳሪ የንግድ ማዕከል ከሆኑ የአፍሪካ ከተሞች ግንባር ቀደም ከተማ ሆና ማየት፡፡
በ2022 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ ዘመናዊ፣ ፍትሃዊና ተወዳዳሪ የንግድ ማዕከል ከሆኑ የአፍሪካ ከተሞች ግንባር ቀደም ከተማ ሆና ማየት፡፡
ተልእኮ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማውን ህብረተሰብ ተሳትፎ በማጠናከር፣ በዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂ በመታገዝ እና የንግድ ምዝገባና ፍቃድ አሰራር በማዘመን፣ ደረጃዎችን የጠበቁ የግብይት ማዕከላትን በማስፋፋት፣ ጠንካራ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት እና የሸማቾችን መብትና ጥቅም በማስጠበቅ ፍትሃዊ ግብይትን ማስፈን፤
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማውን ህብረተሰብ ተሳትፎ በማጠናከር፣ በዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂ በመታገዝ እና የንግድ ምዝገባና ፍቃድ አሰራር በማዘመን፣ ደረጃዎችን የጠበቁ የግብይት ማዕከላትን በማስፋፋት፣ ጠንካራ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት እና የሸማቾችን መብትና ጥቅም በማስጠበቅ ፍትሃዊ ግብይትን ማስፈን፤
እሴት
• መብቃት/ማብቃት
• ተግባራዊነት
• ሙያዊነት
• ሥነ-ምግባራዊነት
• መልካም ስብዕና
• አዎንታዊነት
• ትብብርና ቅንጅት
• የቴክሎጂ ተጠቃሚነት
Heads of Government Ethiopia
Abiy Ahmed Ali : Abiyi Ahmed Alii; Amharic: ዐቢይ አሕመድ ዐሊ; born 15 August 1976) is an Ethiopian politician serving as the third Prime Minister of Ethiopia since 2018, and as the leader of the Prosperity Party since 2019.[1][2] He was awarded the 2019 Nobel Peace Prize “for his efforts to achieve peace and international cooperation, and in particular for his decisive initiative to resolve the border conflict with neighbouring Eritrea“..
The president of Ethiopia is the head of state of Ethiopia. The position is largely ceremonial with executive power vested in the Council of Ministers chaired by the prime minister. The current president Taye Atske Selassie Amde (Amharic: ታዬ አጽቀሥላሴ, born 13 January 1956) is an Ethiopian diplomat and politician who is serving as president of Ethiopia since 7 October 2024. He has worked as ambassador on numerous occasions in the United Nations. Prior to assuming this role, he served as the Minister of Foreign Affairs.
Adanech Abebe : Adaanach Abeebee) is an Ethiopian politician and attorney who is serving as the thirty-second mayor of Addis Ababa since 2021. She has been serving as a deputy mayor from 2020 until 2021. She previously was the Minister of Revenue and Customs Authority from 2018[1][2] to 2020, when she became the first female to assume the role of the Federal Attorney General of Ethiopia.[3][4][5][6] She is the first woman to hold the mayorship since it was created in 1910.[