በክ/ከተማው የሚገኙ ነጋዴዎችና የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች የተለያዩ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
በክ/ከተማው የሚገኙ ነጋዴዎችና የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች የተለያዩ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
ኮልፌ ኮሙዩኒኬሽን ሰኔ 27/2018 ዓ ም
በኮልፌ ቀራኒዮ በሚገኙ የሰንበት ገበያዎች የፍጆታ እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለሸማቹ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያውን የማረጋጋት ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በገበያዎቹ አምራች ነጋዴዎችና የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት የተለያዩ ምርቶችን ለህብረተሰቡ እስከ 20% በሚሆን ቅናሽ ዋጋ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ገበያ ማረጋጋትና ህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ግብረ-ኃይል ሰብሳቢና የክ/ከተማው ዋና ስራ አሰፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል፤የክ/ከተማው ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አከበረኝ ወጋገን እና ሌሎች የግብረ-ኃይሉ አባላት በገበያዎቹ ተዟዙረው በቂ ምርት መኖሩን አረጋግጠዋል።
የዝግጅት ክፍላችን ሲገበያዩ አግኝቶ ያነጋገራቸው ሸማቾች በሰጡት አስተያየት የሰንበት ገበያዎች የተለያዩ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ በማድረግ የኑሮ ውድነት ጫናን ከመቀነስ አንፃር ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ገልፀውልናል።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የገበያ ማዕከላት የምርት አቅርቦቱ በተሻለ ጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የገበያ ማዕከላት የምርት አቅርቦቱ በተሻለ ጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ሀምሌ:-04/2018ዓ.ም
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 21 የቅዳሜና እሁድ ገበያ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላት እንዲሁም የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች ያሉ ሲሆን የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስና የገበያ ማረጋጋት ተግባሩን እውን ለማድረግ የምርት አቅርቦቱ በዛሬው እለትም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።
በሁሉም የገበያ ማዕከላት የግብርና ምርቶች እንዲሁም የእንስሳት ተዋዕፆና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣጣኝ ዋጋና በተሻለ ጥረት እየቀረቡ ሲሆን ነዋሪዎች በአካባቢያቸው በሚገኙ የገበያ ማዕከላት በመሸመት ካላስፈላጊ የዋጋ ጭማሬና የትራንስፖርት ወጪ ብክነትን እንዲቆጥቡ የማድረጉ ተግባር እንደቀጠለ ነው።
የክፍለ ከተማ አስተዳደሩም የቅዳሜና እሁድ ገበያ የምርት አቅርቦት ስራው ሳይቆራረጥ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማስቀጠል በትኩረት ይዞ እየሰራ ሲሆን ነዋሪው ማህበረሰብ ካላስፈላጊ የዋጋ ጭማሬና ከህገወጥ ነገዴዎች እራሱን በመከላከል በገበያ ማዕከላቱ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ስርዓት ከጊዜ ወደጊዜ ለማሳደግ ያለው ቅንጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በክፍለ ከተማው አስተዳደር የቅዳሜና እሁድ ገበያ ማዕከላት የምርት አቅርቦት ሂደቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በ21ዱም የቅዳሜና እሁድ ገበያ ማዕከላት የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ምርቶች በበቂ ሁኔታ በተመጣጣኝ ዋጋ ቀርበዋል።
በቀን 13-14/2018 ዓ.ም የመሸጫ ዋጋ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል ነዋሪዎቻችን በአቅራቢያችሁ በሚገኘው የገበያ አማራጭ በተጠቀሰው ዋጋ ኑ ሸምቱ በማለት የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ጥሪውን አቅርቧል።
በክፍለ ከተማው አስተዳደር የቅዳሜና እሁድ ገበያ ማዕከላት የሚቀርቡ ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁና በዋጋ ተመጣጣኝ በመሆናቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገለፁ።
በክፍለ ከተማው አስተዳደር የቅዳሜና እሁድ ገበያ ማዕከላት የሚቀርቡ ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁና በዋጋ ተመጣጣኝ በመሆናቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገለፁ።
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ሰኔ 13 /2018 ዓ.ም
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቅዳሜና እሁድ ገበያ አገልግሎት የሚሰጡ የገበያ ማዕከላት የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስና የገበያ ማረጋጋት ሂደቱን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ምርቶች በተሻለ ጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ በመሆኑ ተጠቃሚ መሆናቸውን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት በቅዳሜና እሁድ ገበያ ማዕከላት የሚቀርቡ ምርቶች የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስና የገበያ ማረጋጋት ሂደቱን ተጨባጭ ከማድረግ አንፃር ያሉ ለውጦችን በሚመለከት ተጠቃሚዎችን አነጋግሯል።
ተጠቃሚዎችም እንደገለፁት በቅዳሜና እሁድ ገበያ ማዕከላት የሚቀርቡ፣የግብርናነ የኢንዱስትሪ ምርቶች ጥራታቸውና አቅርቦታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉ መምጣታቸውና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው በመሆኑ ተጠቃሚ መሆን ችለናል ሲሉ ተናግረው የቁጥጥርና ክትትል ስራው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የገበያ ማረጋጋት ስራውን በትኩረት በመያዝ የሚቀርቡ ምርቶች በተሻለ ጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ወደ ተጠቃሚዎች ለማድረስ በእቅድ የሚመራ ተቋማዊ አሰራርን ተግባራዊ በማድረግ አልፎ አልፎ የሚከሰት የምርት እጥረቶችንም ጭምር አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት እየተሰራ መሆኑንና በቀጣይም በቅንጅት በከፍተኛ ትኩረት የኑሮ ውድነቱን ለማሻሻል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ያሲን መሀመድ ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማ አስተዳደሩም የቅዳሜና እሁድ ገበያ ማእከላት የተለያዩ የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን በስፋት ማቅረቡን አጠናክሮ ቀጥሏል።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በቅዳሜና እሁድ ገበያ ማዕከላት የሚያቀርባቸው ምርቶች ተመጣጣኝ ዋጋና የተሻለ ጥራት እንዲኖራቸው በማድረግ የምርት አቅርቦት ሂደቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ሰኔ 20 /2018ዓ.ም
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቅዳሜና እሁድ ገበያ አገልግሎት የሚሰጡ የገበያ ማዕከላት እንዲሁም የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች ያሉ ሲሆን የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስና የገበያ ማረጋጋት ተግባሩን እውን ለማድረግ የምርት አቅርቦቱ በዛሬው እለትም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።
በሁሉም የገበያ ማዕከላት የግብርና ምርቶች እንዲሁም የእንስሳት ተዋዕፆና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ ሲሆን ነዋሪዎች በአካባቢያቸው በሚገኙ የገበያ ማዕከላት በመሸመት የጊዜ፣ የጉልበትና የገንዘብ ብክነትን እንዲቆጥቡ የማድረጉ ተግባር እንደቀጠለ ነው።
የክፍለ ከተማ አስተዳደሩም የቅዳሜና እሁድ ገበያ የምርት አቅርቦት ስራውን በትኩረት በመያዝ ነዋሪው ማህበረሰብ ካላስፈላጊ የዋጋ ጭማሬና ከህገወጥ ነገዴዎች እራሱን በመከላከል በገበያ ማዕከላቱ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ስርዓት ከጊዜ ወደጊዜ ለማሳደግና የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።